loading
በኮምቦልቻ በደረሰ የመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ

አርትስ ታህሳስ 12 2011

በትናንትናው ዕለት በኮምቦልቻ ከተማ በተለምዶ ማርያም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባትሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡

አደጋው የቀን ሰራተኞችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የጭነት አይሱዙ መኪና በመገልበጡ የተከሰተ ሲሆን ቁጥራቸው ያልታወቁሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል ።

አደጋው ምሽት አንድ ሰዓት ላይ የተከሰተ መሆኑን የገለጹት የኮምቦልቻ ከተማ የመንገድ ደህንነት የስራ ሂደት ባለቤትምክትል ኮማንደር ወሰን አሰፋ በአደጋው የሟቾቹ ቁጥር ሊጨምር ይችላል ብለዋል።

ተሸከርካሪው በአጠቃላይ 50 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ እንደነበርም ምክትል ኮማንደሩ ጠቅሰዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *