loading
የቀድሞው የሞሳድ አለቃ ሞስኮ በ2016ቱ የአሜሪካ ምርጫ ጣልቃ መግባቷን አጋለጡ

እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር 2011 እስከ 16 የእስራኤል የስለላ ድርጅት (ሞሳድ) ዳይሬክተር የነበሩት ታማር ፓርዶ በ2016 የአሜሪካ ምርጫ የፑቲን እጅ እንደነበረበት ተናግረዋል፡፡

“ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ሰተት ብለው እንዲገቡ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን መንገዳቸውን እንዳመቻቹላቸው አውቃለሁ”  ብለዋል የቀድሞው የስለላ ተቋም ሀላፊ፡፡

ዋሽንግተን ለምርጫ ደፋ ቀና ስትል የክሬምሊን ሰዎች ደግሞ ማን ወደ ስልጣን ቢመጣ ተጠቃሚ እንሆናል እያሉ ሌት ተቀን ይመክሩ ነበር ፡፡

የእስራኤሉ ደይሊ ሀራትዝ እንደዘገበው የፑቲን አስተዳደር ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው ቢያሸንፉ ሩሲያ ፖለቲካዊ ትርፍ እንደምታገኝ ካረጋገጠ በኋላ ሂላሪ ክሊንተን ከጨዋታ ውጭ እንዲሆኑ የቤት ስራውን በሚገባ ተወጥቷል፡፡

ፓርዶ እንደሚሉት ሩሲያ የምርጫውን ሂደት በቀጥታ የምትከታተልበት ሲስተም በመዘርጋት  እያንዳንዷን መረጃ በእጇ ታስገባ ነበር፡፡

የአሜሪካ የደህንነት ሰዎች ሩሲያ  የምርጫው ሚዛን ወደ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዲያጋድል ለማድረግ የሳይበር ጥቃት  መፈፀሟን ደጋግመው ቢናገሩም ትራምፕ ግን ነገሩን መሰረተ ቢስ በለውታል፡፡

ሞስኮ ይህን ለማድረግ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኦን ላይን ሮቦቶችን አሰማርታ እንደነበር የሞሳዱ ሰው ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ፑቲን በተለይ ከሪፓብሊካኑ ወገን ለሚደርስባቸው ወቀሳ እኛ በሰው ቤት ምን አገባን እዛው ራሳችሁን ቻሉ የሚል መልስ ነው የሰጡት፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *