loading
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሕግና ፍትህ አማካሪ ጉባዔ አባላትን አወድሱ

አርትስ 18/04/2011

ጠቅላይ ሚኒስትር  ዓቢይ አህመድ የሕግና ፍትህ አማካሪ ጉባዔ አባላትን ያመሰገኑት ትናንት በፅ/ቤታቸው ከአባላቱ ጋር በተወያዩበት ጊዜ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን የቸሩት የጉባዔው አባላት የሕግ ማሻሻያዎችን በመከለስና ምክረ ሃሳብ በመስጠት ላደረጉት የነፃ አገልግሎትነው።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በተገኘው መረጃ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ  አህመድ እንደ የፀረ-ሽብርና የሲቪል ማህበራት ባሉ የሕግማዕቀፎች ላይ የሚደረጉ ማሻሻያዎች፤ የሕግ የበላይነትን ሳይጋፉ የዜጎችን መብትና ነፃነት እንዲያስከብሩ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የሕግና ፍትህ አማካሪ ጉባዔ ከአራት ወራት በፊት በፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መዋቀሩ የሚታወስ ሲሆን በተለያዩ የሀገሪቱ ህጎች ላይ ማሻሻያ እንዲደረግባቸው እየተንቀሳቀሱ ይገኛል።መረጃዉን ያገኘነዉ ከጠቅላይ ሚኒስቴር  ጽ/ቤት ነዉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *