loading
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ድል ተመልሷል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ድል ተመልሷል

አርትስ ስፖርት 19/04/2011

በሦስተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መካሄድ የነበረበት የተስተካካይ መርሃግብር ጨዋታ፤ ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ጅማ አባ ጅፋር መካከል ተካሂዷል፡፡

በጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጉዳት የተመለሰለትን አጥቂውን ሳላዲን ሰዒድ ይዞ ገብቷል። ጨዋታው በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ፍጥነት ቢኖረውም በዚሁ ግን መቀጠል አልቻለም። ፈረሰኞቹ ተጭነው በመጫወት በተለያዩ አጋጣሚዎች የግብ ሙከራዎችን ግን አድርገዋል። እነዚሁ ሙከራዎች በሳላዲን ሰዒድ እና አቡበከር ሳኒ ተደርገዋል።

ኋላቸውን ጠብቀው የተጫወቱት ጅማ አባ ጅፋር ግልፅ የሚባሉ ባይሆኑም አንዳንድ የግብ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል። የመጀመሪያ አጋማሽ አንዳንዴ ከሚታዩ የግብ ሙከራዎች ውጭ ይህን ያህል ከባድ ሙከራዎችን ሳያስተናግድ ያለጎል ተጠናቋል።

በሁለተኛው አጋማሽ ጅማዎች ቢስማርክ አፒያን ቀይረው ወደ ሜዳ በማስገባት ወደ ግብ ሲደርሱ ቢታይም  መከላከል ላይ ክፍተት መፈጠሩ ተስተውሏል፡፡

በአቤል ያለው የግብ ሙከራ ጫና ማሳየት የጀመሩት ጊዮርጊሶች በስምንት ደቂቃዎች ልዩነት ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል። የመጀመሪያው ግብ ወጣቱ አቤል ያለው በ56ኛው ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥር ከአጃዬ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ ከመረብ አዋህዷል። ሁለተኛዋን ግል ደግሞ በ62ኛው ደቂቃ ከአቤል ያለው የተሻገረችውን ኳስ ሳላዲን ሰዒድ ከመረብ አገናኝቷል። ከፈረሰኞቹ መሪነት በኋላ በቀሪዎቹ ደቂቃዎች ጅማ አባ ጅፋር ከአፒያ ኢላማውን ያልጠበቀ ሙከራ ሌላ አላደረገም፡፡

ባለሜዳው ጊዮርጊስ በሳላዲን እና አቡበከር አማካኝነት ሙከራዎችን አድርገዋል። ሙሉ ጨዋታውም በቅዱስ ጊዮርጊስ

2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። በሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ5 ጨዋታ ስምንት ነጥቦችን ሰብስቦ 7ኛ ደረጃ ላይ ተገኝቷል፤ ሦስት ጨዋታዎችን ብቻ ያከናወነው ጅማ አባ ጅፋር በ4 ነጥቦች 13ኛ ላይ ተቀምጧል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *