loading
ፊሊፒንስ ባጋጠማት የመሬት መንሸራተት የሟቾች ቁጥር ጨምሯል

ፊሊፒንስ ባጋጠማት የመሬት መንሸራተት የሟቾች ቁጥር ጨምሯል

በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ቢኮል እና ቪሳያስ በተባሉ አካባቢዎች የተከሰተው የጎርፍ አደጋ እና የመሬት መንሸራተት  75 ሰዎችን ገድሏል፡፡

የሀገሪቱ ብሄራዊ የአደጋ ቅነሳ ቢሮ እንዳስታወቀው ከሞቱት በተጨማሪ 16 ሰዎች እስካሁን የገቡበት አልታወቀም ፡፡

ለአብዛኞቹ ሞት ምክንያት የሆነው የመሬት መንሸራተት አደጋው ሲሆን  የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የጠፉትን ሰዎች በማፈላለግ ተግባር ላይ እንደተጠመዱ ናቸው፡፡

ዘ ኢንዲፔንደንት እንደዘገበው አደጋዎቹ በተከሰቱባቸው አካባቢዎች 40 ሺህ ነዋሪዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ለመፈናቀል ግድ ሆኖባቸዋል፡፡

አደጋው በፈጠረው ስጋት ሳቢያ የአየርና የባህር ጉዞዎች በመሰረዛቸው በሺዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች እየተጉላሉ እንደሚገኙም ተነግሯል፡፡

ፊሊፒንስ በየዓመቱ ከ20 በላይ ተመሳሳይ አደጋ የሚገጥማት ሲሆን በጣም አስከፊ የሚባለው አደጋ የደረሰባት ግን  እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2013 ስድስት  ሺህ 300 ሰዎችን የገደለው እና 4 ሚሊዮን ዜጎች የተፈናቀሉበት ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *