loading
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክር ወርቅነህ ገበየሁ በትናንትናው ዕለት በሱዳን ካርቱም የስራ ጉብኝት አድርገዋል

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክር ወርቅነህ ገበየሁ በትናንትናው ዕለት  በሱዳን ካርቱም የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ከፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ጋር በኢትዮጵያ እና በሱዳን ያለውን ወዳጅነት እና ዝምድና የበለጠ መጠናከር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ፕሬዝዳንት አልበሽር ሱዳን ውስጥ የሚገኙ ዜጎች እንደ አገራቸው እንዲሰማቸው እናደርጋለን ብለዋል፡፡
ዶክተር ወርቅነህም መንግስት ለዜጎች ደህነነት መረጋገጥ፣ ክብራቸው መጠበቅ ትኩረት እንደሚሰጥ ተናግረው ፕሬዝዳንት አልበሽር ከወራት በፊት በርካታ ኢትዮጵያውያን እስረኞች በምህረት እንዲፈቱ በማደረጋቸው አመስግነዋቸዋል፡፡

ዶክተር ወርቅነህ በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ኮሚኒቴ ድጋፍ የሚደረግላቸውን ኢትዮጵያውያን ጎብኝተዋል፤ ኢትዮጵያውያኑ በቁጥር ከ 30 በላይ ሲሆኑ በኤምባሲው ጊዜያዊ ማቆያ ጉዳት የደረሰባቸው ያገግማሉ፤ አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸውም ህክምና ይደረግላቸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *