loading
በቦሌ ክፍለ ከተማ በጦር መሳሪያ የተደገፈ ዘረፋ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ፡፡ 

በቦሌ ክፍለ ከተማ በጦር መሳሪያ የተደገፈ ዘረፋ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀዉ ቁጥራቸው 24 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች ማክሰኞ ከሌሊቱ 7፡20 የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 30212 ኦ/ሮ አይነቱ ሚኒባስ በሆነ ተሸከርካሪ ተሳፍረው ወንጀል ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ ፤ፖሊስ አስቀድሞ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት እና ባደረገው ክትትል በቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ስፍራው ሰሚት ሴንተራል ሆቴል አካባቢ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡

የሰሚት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ም/ኮማንደር ካሳሁን ፍቃዱ እንደተናገሩት ተጠርጣሪዎቹ በተያዙበት ወቅት አንድ ሽጉጥ ከመሰል ስምንት ጥይት ጋር ፣ ሁለት ፓውዛ መብራቶች ፣ የብረት መቁረጫ መቀስ ፣ 20 ማዳበሪያዎች እና ከተር በኢግዚቢትነት ተይዞ ፖሊስ ምርመራውን አጠናክሮ መቀጠሉን ከኃላፊው ገለፃ መረዳት ተችሏል፡፡

ከዚህ ቀደም በቦሌ ክፍለ ከተማ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ለግንባታ የሚውሉ ልዩ ልዩ የኤሌትሪክ ገመዶችን የሰረቁ ተጠርጣሪዎች በህብረተሰቡ ትብብር ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ም/ኮማንደር ካሰሁን ተናግረው ፤ለፖሊስ ስራ ስኬታማነት ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ቀና ትብብር አድንቀዋል፡፡

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *