loading
የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታዎች ዛሬና ነገ በርከት ብለው ይካሄዳሉ

የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታዎች ዛሬና ነገ በርከት ብለው ይካሄዳሉ

የኢምሬትስ ኤፍ ኤ ካፕ ሶስተኛ ዙር ግጥሚያዎች ትናንት መካሄድ ጀምረዋል፤ ቶተንሃም ከሜዳው ውጭ በሊግ 2 ተሳታፊ የሆነውን ትራንሜሬ የ7 ለ 0 ሽንፈት አከናንቦታል፡፡ በጨዋታው ፈርናንዶ ሎሬንቴ ሀትሪክ ሲሰራ ሰርጂ ኡርዬ ሁለት እንዲሁም ሰን ሂንግ ሚንና ሀሪ ኬን ቀሪዎቹን ከመረብ አገናኝተዋል፡፡
ዛሬ በርካታ ጨዋታዎች ሲከናወኑ፤ 9፡30 በኦልትራፎርድ ማንችስተር ዩናይትድ ከ ሬዲንድ፣ በርንማውዝ ከ ብራይተን፣ ዌስት ሃም ከ በርሚንግሃም፣ በርንሌ ከ ባርንስሌ፤ እንዲሁም አመሻሽ 12፡00 ሲል በስታንፎርድ ብሪጅ ቼልሲ ከ ኖቲንግሃም ፎሬስት፣ ኢቨርተን ከ ሊንኮልን ሲቲ፣ ደርቢ ከ ሳውዛምፕተን፣ ግሊንግሃም ከ ካርዲፍና አስቶን ቪላ ከ ስዋንሲ ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
ምሽት 1፡30 ብላክፑል ከ አርሰናል፣ ብሪስቶል ሲቲ ከ ሀደርስፊልድ፣ ክሪስታል ፓላስ ከ ግሪምስቢ፣ ኒውካስትል ከ ብላክበርን ይጫወታሉ፡፡
ነገ በ11፡00 ኢቲሃድ ላይ ማንችስተር ሲቲ ከ ሮዘርሃም፣ ፉልሃም ከ ኦልድሃም፣ ወኪንግ ከ ዋትፎርድ ሲገናኙ፤ 1፡30 ሲል ኒውፖርት ከ ሌስተር ሲቲ ይፋለማሉ፤ ሰኞ ደግሞ ወልቭስ ምሽት 4፡45 ሊቨርፑልን ያስተናግዳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *