loading
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያን በወጭ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ቀዳሚ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራሁ ነው አለ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያን በወጭ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ቀዳሚ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራሁ ነው አለ

ሚኒስቴሩ ይህን ያለው በሚኒስቴሩ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ደዋኖ ከድር መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ ሚሲዮኖች ጋር በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት እድሎች ዙሪያ በጽህፈት ቤታቸው በተወያዩበት ወቅት ነው።

በውይይቱ አምባሳደር ደዋኖ ኢትዮጵያ የብዙ አገራት የንግድ እና የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗን ጠቅሰው በርካታ አገራት መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ በአገሪቱ እድገት፣ በስራ ፈጠራ እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት እንዳስታወቀው፤ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የንግድና ኢንቨስትመንነት እምቅ አቅም እንዳላት፤ በዘርፉም የሚሰተዋሉ የአሰራር ክፍተቶች እና ቅሬታዎችን ለመፍታት እንዲሁም ተጠቃሚ ለመሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሚኒስቴሩ እንደሚሰራ አምበሳደር ደዋኖ ከድር አብራርተዋል።

በውይይቱ ከተሳታፊ የሚሲዮኖች ተወካዮች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *