loading
ላልይበላን በቀንና በማታ መጎብኘት የሚያስችል የአረንጓዴ ብርሃን ቴክኖሎጂ ሊተገበር ነው ተባለ

ላልይበላን በቀንና በማታ መጎብኘት የሚያስችል የአረንጓዴ ብርሃን ቴክኖሎጂ ሊተገበር ነው ተባለ፡፡

ከፍተኛ የቱሪዝም ፍሰትን የሚጨምር ነው የተባለው ይኸው ቴክኖሎጂ ተግባራዊ የሚደረገው ከአየር ላንድ መንግስት ጋር በመተባበር ነው።

የአየር ላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናትን በጎበኙበት ወቅት የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው እንዳሉት ቴክኖሎጂው በአክሱም ፣ሐረር እና አዲስ አበባ ላይ ተግባራዊ ይደረጋል።

የአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር እንደተናገሩት አየር ላንድ በባህላዊ ቅርስ ቱሪዝም ዙሪያ የካበተ ልምድ ስላላት እሱን ከመጪው ግንቦት እና ሰኔ ወር ጀምሮ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ጋር በጋራ ለመስራት ትብብር እንፈራረማለን ብለዋል ።

የአየር ላንድ መንግስት ከባህል እና ቱሪዝም ጋር በመተባበር እ.ኢ.አ ከ2019-2021 ድረስ የሚቆይ ባህላዊ ቅርሶች እና በገጠር ቱሪዝም ላይ አብረው እንደሚሰሩም ተነግሯል።

የአየር ላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር የላሊበላ ጉብኝታቸውን አጠናቀው አክሱም የገቡ ሲሆን በቀጣይም የሽሬ አዲሀርሽ የስደተኞች መጠለያን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *