ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የሰበታ ዓይነ ስውራን ትምህርት ቤትን ገበኙ።
ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የሰበታ ዓይነ ስውራን ትምህርት ቤትን ገበኙ።
በጉብኝቱ ወቅትም በትምህርት ቤቱ አሉ በተባሉ ችግሮች ዙሪያ እና በመፍትሄዎቻቸው ላይ ምክክር አድርገዋል።
በውይይቱ ላይ የተማሪዎች ማደሪያ ክፍል የትምህርት ቁሳቁስ፣ የተማሪዎች ወንበር እና የቤተ ሙከራ መሳሪያዎች እንዲሁም የህክምና ተቋም ቸግሮች ተነስተዋል።
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በውይይቱ ወቅት በተነሱ ችግሮች ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት መፍትሄ እንዲሰጠው አደርጋለሁ ብለዋል።
የሰበታ ዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት በ1956 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅትም 256 ዓይነ ስውራን ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል ዋልታ እንደዘገበው።