loading
የከተራና የጥምቀት በዓላት በሰላም መከበራቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የከተራና የጥምቀት በዓላት በሰላም መከበራቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ህብረተሰቡ ላደረገው ቀና ትብብር ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

በሀገራችን በርከታ ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት ከሚያከብራቸው ሃይማኖታዊ በአላት መካከል የከተራና የጥምቀት በአላት ይገኙበታል፡፡

እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የኃይማኖቱ ተከታዮች ፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ መቀመጫቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ ያደረጉ የውጪ ሀገራት ዲፕሎማቶች እና የተለያዩ ሀገራት ቱሪስቶች በስፋት የታደሙበት በአዲስ አበባ በልዩ ልዩ ስፍራዎች በተለይም በጃን ሜዳ የተከበሩት የከተራና የጥምቀት በዓላት በሰላም መከበራቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በያዝነው ዓመት በርካታ ህዝብ የታደመባቸው ሃይማኖታዊ እና ስፖርታዊ ዝግጅቶች በሰላም መከበራቸውን ኮሚሽኑ አስታወሶ የዘንደሮ የከተረና የጥምቀት በዓለት በሰላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ በዋናነት ደግሞ የከተማችን ወጣቶች ለሰላማችን መረጋገጥ እያበረከቱት ላለው ቀና ትብብር ምስጋናውን  አቅርቧል፡፡

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *