loading
አዝመራ ሽሮና ሴንቸሪ አዲስ ሪል እስቴት የዉሃ ቆጣሪን በማንሳት ያለቆጣሪ የዉሃ አገልግሎት ሲጠቀሙ በመገኘታቸዉ ተቀጡ፡፡

አዝመራ ሽሮና ሴንቸሪ አዲስ ሪል እስቴት የዉሃ ቆጣሪን በማንሳት ያለቆጣሪ የዉሃ አገልግሎት ሲጠቀሙ በመገኘታቸዉ ተቀጡ፡፡
በተለምዶ ሀያሁለት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የንግድ ስራ የሚያከናውነው አዝመራ ሽሮ ተብሎ የሚጠራው ድርጅት እና ቦሌ አትላስ አካባቢ የሚገኘው ሴንቸሪ አዲስ ሪል እስቴት የተባለው ተቋም በህገወጥ መንገድ የውሃ ቆጣሪ በማንሳት ለባለስልጣኑ ይገባ የነበረውን ገቢ በማስቀረታቸው እርምጃ እንደተወሰዳቸባቸዉ የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ገለጸ፡፡

የባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን የስራሂደት መሪ ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸዉ ለአርትስ እንደተናገሩት   ህገወጥ ድርጊቱን ፈጻሚዎቹ በቀን ሊጠቀሙ የሚችሉትን አማካይ ፍጆታ እና ለምን ያህል ጊዜ ድርጊቱን እንደፈጸሙ በማስላት አዝመራ ሽሮ በ165 ሺህ 689 ብር እንዲሁም ሴንቸሪ አዲስ ሪል እስቴት 126 ሺህ 137 ብር እንዲከፍሉ ተወስኗል ፡፡
ባለስልጣኑ በቀጣይ መሰል ህገወጥ ድርጊቶችን ለመከለከል በቁርጠኝነት አየሰራ እንደሆነም ሰምተናል፡፡
ባለስልጣኑ በሌሎች አካባቢዎችም መሰል ተግባር የሚፈጽሙ አካላት ላይ እርምጃ ለመውስድ የማጣራት ስራ እየተሰራ ሲሆን፤
ደንበኞችም በህገወጥ ተግባር ውስጥ ከመሳተፍ በመቆጠብና ህገወጥ አከላት በመጠቆም ውስን የሆነውን የውሃ ሀብት ከብክነት በመከላከል የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ አሳስቧል፡፡

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *