በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋር የነበረ ብርድልብስ በቁጥጥር ሥር ዋለ፡፡
በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋር የነበረ ብርድልብስ በቁጥጥር ሥር ዋለ፡፡
በትላንትናዉ ዕለት ግምታዊ ዋጋው 200ሺህ ብር የሆነ ህገ-ወጥ ብርድልብስ በቁጥጥር ሥር መዋሉን በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
ቅ/ጽ/ቤቱ እንደገለጸው፤ ጥር 19/2011 ዓ.ም ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት የሰሌዳ ቁጥሩ 57675 ኦሮ የሆነ ተሽከርካሪ ከጅግጅጋ ወደ ሀረር በመጓጓዝ ላይ እንዳለ በጉምሩክና በክልሉ አድማ ብተና አካላት በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡
የመኪና አሽከርካሪው ለጊዜው ስላመለጠ ቅ/ጽ/ቤቱ ክትትል እያደረገ ሲሆን ማህበረሰቡም ለሕግ በማቅረብ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል፡፡
ምንጭ ፤-ገቢዎች ሚኒስቴር