loading
ሰዎች ለሰዎች “People to people” የተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት በጤና ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላባረከቱ 4 ኢትዮጵያውያን ሽልማት ሰጠ።

ሰዎች ለሰዎች “People to people” የተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት በጤና ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላባረከቱ 4 ኢትዮጵያውያን ሽልማት ሰጠ።

የጤና ባለሙያዎች፣ የፊዚክስ ባሙያዎችና ሌሎች ሙያተኞች አባል የሆኑበት ድርጅቱ ከ25 አመት በፊት አሜሪካን ሀገር በሚኖሩ የጤና ባለሙያዎች ነው የተመሰረተው። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ “ወጣት፣ አዳጊ ኮከብ መሪ” (Young rising star award) ሽልማት የተሰጣቸው በጤናው ዘርፍ በግላቸው ጭምር ላበረከቱት አስተዋፅኦ ነው።

በወጣት ባለሙያዎች የዘረጉት “የጥቁር አንበሳ የተቀናጀ የህክምና አስተዳደር ስርዓት” ለሽልማት ካበቃቸው ስራ ውስጥ ተጠቃሽ ነው።

“ሀገሬ ለእኔ ያደረገችልኝን ያክል አላደረኩላትም” ያሉት ሚኒስትሩ በእውቅና ሽልማቱ እንደተደሰቱና ለሀገራቸው ከዚህ የበለጠ ለመስራት እንደሚተጉ ተናግረዋል።

ከእርሳቸው በተጨማሪ 3 ግለሰቦችም ሽልማት አግኝተዋል ፤ዶ/ር ሃይሉ ከፈኔ “የህይወት ዘመን መድሃኒት ህክምና እና የጤና እንክብካቤ ባለሙያዎች እድገት ሽልማት” በሚል የተሸለሙ ሲሆን ለረጅም ጊዜ በጤናው ዘርፍ በርካታ ስራዎችን ሰርተዋል።

ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሴ የሴት ተማሪዎች ህብረት በመመስረት ኤች አይቪ መከላከል ላይ በሰሩት ስራ “የማህበረሰብ አገልግሎት” (Community service award) ተሸላሚ ሆነዋል። በህይወት የሌሉት ወ/ሮ ወደድ ኪዳነማሪያም የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ማህበረን በመመስረት በህክምና ቁሳቁስ አቅርቦትና የህፃናት ጤና ጥበቃ ላይ በሰሩት ስራ የማስታወሻ የእውቅና ሽልማት (posthumous award) ታስቦላቸዋል።

“ፒ ቱ ፒ” በመባል የሚታወቀው ግብረ ሰናይ ድርጅት የኢትዮጵያን የጤና ተቋማት ከአሜሪካ አቻ የጤና ተቋማት ጋር በማስተሳሰር የእውቀት ሽግግር እንዲኖር ማስቻል፣ በኢትዮጵያ ያሉ የጤና ተቋማትን ከምዕራባዊያን ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ማስተሳሰር፣ ኤች አይቪ ላይ፣ ወላጅ የሌላቸው ህፃናት ላይ እና በመሳሰሉት የጤና ጉዳዮች ላይ የሚሰራ ድርጅት ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *