loading
ኩባ በሀገሯ ብቻ  የሚገኙ መድሃኒቶችን በኢትዮጵያ ልታመረት ነዉ፡፡

ኩባ በሀገሯ ብቻ  የሚገኙ መድሃኒቶችን በኢትዮጵያ ልታመረት ነዉ፡፡

ኩባ በቀላል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ነዉ መድሃኒቶችን የማታመርተዉ ተብሏል
በኩባ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ድራ ሲዲ ሳሉደ ማርዚያ የተመራ ልዑክ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች ጋር ወደ ስራ መግባት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
ኩባ የካንሰር በሽታን ባለበት የሚያቆይ መድሃኒት እና እንስሳትን በማጥቃት የሚታወቀውን የመዥገር በሽታን የሚያክም መድሃኒት የሚመረትባት ሀገር ናት፡፡
እነዚህን መድሃኒቶች በኢትዮጵያ ለማምረት ሀገሪቱ በዝግጅት ላይ መሆኗን ልዑካኑ ተናግረዋል፡፡
የመድሃኒት ፋብሪካው በኢትዮጵያ ውስጥ መከፈት የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ፣ የሰው ሃብት ልማት ለመፍጠር እና ኢትዮጵያን የልዩ መድሃኒት ማምረቻ ሀገር ለማድረግ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር  ጌታሁን መኩሪያ ተናግረዋል፡፡

ሀገሪቱ በሌላ አለም የማይገኙና በኩባ ብቻ የሚገኙ የሰው እና የእንስሳት መድሃኒቶችን ኢትዮጵያ ውስጥ በማምረት ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ ገበያ ለማቅረብ ከዚህ በፊት ስምምነት ላይ መድረሷ ይታወቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *