በጅብቲ በደረሰው የጀልባ መገልበጥ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያዉያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰማውን ሐዘን ገልጸ፡፡
በጅብቲ በደረሰው የጀልባ መገልበጥ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያዉያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰማውን ሐዘን ገልጸ፡፡
ጅቡቲ ሰሜን-ምስራቅ አቅጣጫ ኦቦክ በተሰኘች አስተዳደራዊ-ክልል በሚገኘው ጎዶሪያ በተሰኘ ስፍራ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ የመን ለመሸጋገር ሲሞክሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥር 21 ቀን 2011ዓ.ም በደረሰው የጀልባ መገልበጥ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል፡፡
አደጋው ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በጅቡቲ የኢፌዲሪ ኤምባሲ ም/ሚሲዮን መሪ አምባሳደር መሐመድ ሐሰን የተመራ 4 አባላት ያሉት የልዑክ ቡድን አደጋ ወደተከሰተበት የጅቡቲ መንግስት አካላት፣ የዓለም-አቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበርና የስደተኞች ድርጅት(IOM) ሃላፊዎች ጋር የተወያየ ሲሆን በአስተዳዳሪውና በፖሊስ ድጋፍ አደጋው ወደ ተከሰተበትና ከኦቦክ 37 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ጎዶሪያ የተባለ ስፍራ በመሄድ በሕይወት የተረፉትን ሰዎች አነጋግሯል፡፡
አደጋው በደረሰበት አካባቢ በመገኘት ከጅቡቲ መንግስትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመገናኘት ስለአደጋውና በቀጣይ መደረግ ስላለባቸው ጉዳዮች የተወያየ ሲሆን ከአደጋው የተረፉት ዜጎቻችንን ጎብኝተዋል፡፡
በመጨረሻም የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሟቾች ቤተሰብ የተሰማውን ሀዘን በመግልፅ መፅናናትን ተመኝቷል፡፡