loading
ኢትዮጵያ ካለባት 26 ነጥብ 791 ቢሊዮን ዶላር እዳ ውስጥ  በስድስት ወር 9 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር መክፈሏ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ካለባት 26 ነጥብ 791 ቢሊዮን ዶላር እዳ ውስጥ  በስድስት ወር 9 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር መክፈሏ ተገለጸ

የገንዘብ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ከፍተኛ የዕዳ ጫና ካለባቸው የዓለም ሃገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ካለባት አጠቃላይ የውጭ እዳ ውስጥ 9 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብሩን የከፈለችው ባለፉት ስድስት ወራት ነው።

የሚኒስቴሩን የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ በተሰጠው መግለጫ እንደተነገረው በተያዘው በጀት ዓመት ሚኒስቴሩ 22 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ያህል የውጭ ዕዳ ለመክፈል ዕቅድ ይዟል።

ከዕዳው 57 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆነው የማዕከላዊ መንግስቱ ሲሆን፥ ቀሪው የልማት ድርጅቶች መሆኑም ተገልጿል።

እንደመግለጫው ኢትዮጵያ ባለባት የዕዳ መጠን ከአውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር 2015 በፊት ዝቅተኛ የብድር ጫና ውስጥ ያለች ሃገር በሚል ደረጃ ውስጥ የነበረች ሲሆን ከ2015 አጋማሽ ጀምሮ ደግሞ መካከለኛ የእዳ ጫና ውስጥ ገብታለች።

ከታህሳስ 2018 ጀምሮ ከፍተኛ የእዳ ጫና ካለባቸው ሃገራት ዝርዝር ውስጥ  መግባቷም ተነግሯል።

መንግስትን ከዚህ ዕዳ ለማላቀቅም በበጀት ዓመቱ እቅዱን ለማሳካት ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል።

እንደሚኒስቴሩ መግለጫ የሀገሪቱን የእዳ ጫና ካከበዱት ጉዳዮች አንዱ  ከሀምሌ 2010 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አምስት ወራት የወጭ ንግድ 977 ነጥብ 6 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ብቻ መሆኑ ነው።

ሃገሪቱ ያለባትን የእዳ ጫና ለመቀነስ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በሙሉ አቅማቸው በማምረት የውጭ ምንዛሬ እንዲያስገኙ ማድረግ የመንግስት ቀጣይ ትኩረት ይሆናል ተብሏል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *