loading
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ምሽት ማንችስተር ሲቲ ከቼልሲ ይፋለማሉ

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ምሽት ማንችስተር ሲቲ ከቼልሲ ይፋለማሉ

የ26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትናንት ሲጀመሩ በቀዳሚው ግጥሚያ ወደ ለንደን ያቀናው ማንችስተር ዩናይትድ ፉልሃምን በፖግባ 2× እና ማርሽያል እና ጎሎች 3 ለ 0 ረትቷል፡፡
ምሽት 12፡00 በተመሳሳይ አምስት ጨዋታዎች ሲደረጉ፤ ሊቨርፑል አንፊልድ ላይ ቦርንመዝን በሳድዮ ማኔ፣ ዊናልደምና ሳላህ ባስቆጠሯቸው ሶስት ጎሎች አሸንፏል፡፡
የኡናይ ኢምሪው አርሰናል ጆን ስሚዝ ላይ ሀደርስፊልድ ታውንን 2 ለ 1 ሲረታ ኢዎቢና ላካዜት የግቦቹ ባለቤቶች ናቸው፡፡
በሌሎች ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ 1 ለ 1 ዌስት ሃም፣ ሳውዛምፕተን 1 ለ 2 ካርዲፍ፣ ዋትፎርድ 1 ለ 0 ኢቨርተን፣ ብራይተን 1 ለ 3 በርንሊ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ሲደረጉ የሳምንቱ ተጠባቂ ግጥሚያ ኢቲሃድ ላይ በማንችስተር ሲቲ እና ቼልሲ መካከል ይከናወናል ምሽት 1፡00 ሲል ያከናወናል፡፡ ሲቲ የውድድር ዓመቱ ያለመሸነፍ ጉዞው የመጀመሪያ ሽንፈት አሀዱ ያለው የማውሪዚዮ ሳሪው ቡድን ሲሆን በዚህም ጨዋታ ፈታኝ ፍልሚያ ይጠብቀዋል፡፡ የሊጉን መሪነት መልሶ ከሊቨርፑል ለመረከብ የግድ ውጤቱ ያስፈልገዋል፡፡
በዕለቱ አስቀድሞ ቀን 10፡30 ቶተንሃም ሆትስፐር በዌምብሌይ ከሌስተር ሲቲ ይገናኛል፤ ሰኞ በሊጉ የሳምንቱ ማሳረጊያ ግጥሚያ ወልቭስ ከኒውካስትል ዩናይትድ ምሽት 5፡00 ላይ ይጫወታሉ፡፡
ሊቨርፑል በሰበሰባቸው 65 ነጥቦች የሊጉ አናት ላይ ተሰይሟል፤ ማን.ሲቲ በ62 ነጥቦች ሁለተኛ ሲሆን ቶተንሃም በ57 ሶስተኛ፣ ማንችስተር ዩናይትድ በ51 አራተኛ፣ ቼልሲ እና አርሰናል ደግሞ በ50 ነጥቦች በግብ ክፍያ ተበላልጠው አምስተኛ እና ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
የሊቨርፑሉ መሀመድ ሳላህ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን በ17 ግቦች እየመራ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *