loading
ታይላንድ አውስትራሊያዊውን አግር ኳስ ተጫዋች ከእስር ነፃ አደረገች

ታይላንድ አውስትራሊያዊውን አግር ኳስ ተጫዋች ከእስር ነፃ አደረገች

ሀገረ ባህሪን ስደተኛዋን እግር ኳስ ተጫዋች ሃኪም አል አራይቢ፤ ተይዞ እንዲመጣላት የማትፈልግ መሆኑን ካስታወቀች በኋላ፤ የታይላንድ መንግስት ተጫዋቹን ከእስር ነፃ ነህ ብሎታል፡፡

ሃኪም አል አራይቢ የባህሪን ዜግነት ቢኖረውም ከሀገሪቱ መንግስት ጋር በመቃቃሩ በ2014 ወደ አውስትራሊያ አግሬ አውጪኝ በማለት ኮበለለ፤ በዚያም ያቀረበው የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ ይሁንታን አገኘ፡፡

በዚህ ሁነት ውስጥ እያለ ከባለቤቱ ጋር ለጫጉላ ሽርሽር ወደ ታይላንድ ባንኮክ ባመራበት በወርሃ ህዳር፤ በባህሪን ጠያቂነት በኢንተርፖል  በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል፡፡

ምክንያቱ ደግሞ ተጫዋቹ በእናት ሀገሩ ፖሊስ ጣቢያን አውክሃል በሚል በተከፈተበት ክስ በሌለበት የ10 ዓመት ዕስር አውጥታበታለችና ነው፡፡

የ25 ዓመቱ አል አራይቢ ግን ክሱን ውድቅ ሲያደርግ፤ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችም ታይላንድ ተጫዋቹን ለባህሪን አሳልፋ የምትሰጠው ከሆነ ስቃይ ይጠብቀዋልና እባክሽ አትጨክኝበት የሚል ውትወታቸውን አሰምተው ነበር፡፡

ትልልቅ ስም ያላቸው እንደነ ዲዲዬ ድሮግባ እና ጃሚ ቫርዲ የመሳሰሉት እግር ኳስ ተጫዋቾች ሀኪም ከእስር ነፃ እንዲደረግ ድጋፋቸውን አሳይተዋል፡፡ የአውስትራሊያ መንግስት፣ የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ፊፋ እና የዓለም ዓቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሁሉም ታይላንድ ሃኪምን ለባህሪን አሰላፋ እንዳትሰጥ ሲያግባቡ ነበር፡፡

የታይላንድ ዋና አቃቢ ህግ ቢሮም፤ የሃኪም አል አራይቢን መዝገብ ፍርድ ቤቱ  እንዲዘጋው መጠየቁንና ከዚህ በኋላም ከተጫዋቹ ጉዳይ የለንም ብለን ተናግረናል ሲሉ ባለስጣናቱ ለቢቢሲ ታይ ዛሬ ተናግረዋል፡፡

የጠቅላይ አቃቢ ህግ ዋና ኃላፊ ቻትኮም አካፒን እንዳሉት ‹‹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ባህሪን ተጫዋቹን የእፈልገዋለሁ ጥያቄ ላይ እጇን በማንሳቷ እንደማይፈለግ ነግረውናል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

አል አራይቢም የታይላንድን ምድር ለቆ ወደ ተጠለለባትና በእግር ኳስ እያገለገላት ወደአለችው ሀገር አውስተራሊያ ዛሬ ያመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከተለያዩ የዓለም ክፍሎችም ይሰሙ የነበሩት ⵌSave Hakeem የዘመቻ መርሀግብር በመጨረሻ ፍሬ ማፍራት ችሏል፡፡

የ70 ቀናት የታይላንድ የዕስር ቆይታውንም አጠናቆ የአውስትራሊያን ምድር ሲረግጥ ሞቅ ያለ አቀባበል ይደረግለታል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ቢቢሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *