loading
ግብፅ የዜጎቻቸውን ነጻነት ከሚጋፉት ሀገራት ከቀዳሚዎቹ ተርታ መሆኗ ተነገረ፡፡

ግብፅ የዜጎቻቸውን ነጻነት ከሚጋፉት ሀገራት ከቀዳሚዎቹ ተርታ መሆኗ ተነገረ፡፡

የአሜሪካው ፍሪደም ሃውስ ተቋም ባወጣው አዲስ ሪፖርት ግብፅ ለዜጎቿ ነፃነትን በማረጋገጥ ከ195 ሀገራት መካከል 126ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

ተቋሙ በሪፖርቱ እንዳብራራው ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ሀገራቸውን ሲመሩ ሀይል ያበዛሉ፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ግብፃዊያን በአልሲሲ መንግስት የመረጃ ነፃነታቸውን በእጅጉ ይነፈጋሉ፡፡

በግብፅ የህዝብ ቤተ መጽሀፍት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን ጥናቱን ያካሄደው ተቋም  በምሳሌነት ያነሳል፡፡

እንደ ፍሪደም ሀውስ ሪፖርት ግብፅ እና ስሪላንካ በፈረንረጆቹ 2018 ዜጎቻቸው የኢንተርኔት አገልግሎት እንዳይጠቀሙ በመከልከል ቀዳሚ ሀገራት ሆነዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ግብፁ የፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲን አስተዳደር የሚቃወሙትን ምክንያት ፈልጋ ወደ እስር ቤት በማስገባትም በብዙ ትታማለች፡፡

በአሁኑ ወቅት ግብፅ ከፖለቲካ ጋር በተገናኙ ምክንያቶች እስር ቤት ያስገባቻቸው ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች መኖራቸውን  የሰብዓዊ መብት ተቋማት ይናገራሉ፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *