loading
የቻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ ግጥሚያዎች ዛሬ ምሽት ቀጥለው ይካሄዳሉ፡፡

የቻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ ግጥሚያዎች ዛሬ ምሽት ቀጥለው ይካሄዳሉ፡፡

 

 

የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የ16ቱ ቡድኖች ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር ግጥሚያዎች ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ መካሄድ ጀምረዋል፡፡

 

 

ዛሬ ምሽት ሁለት ግጥሚያዎች የሚደረጉ ሲሆን በተመሳሳይ ምሽት 5፡00 ላይ ይከናወናሉ፡፡

 

በጉጉት የሚጠበቀው የምሽቱ ጨዋታ በእንግሊዙ ሊቨርፑልና እና በጀርመኑ ባየርን ሙኒክ መካከል አንፊልድ ሮድ ስታዲየም ላይ ይካሄዳል፡፡

 

 

በምሽቱ ግጥሚያ ላይ በቀያዮቹ በኩል መመኪያቸው ቨርጂል ቫን ዳይክ በቅጣት፣ ጆ ጎሜዝ በጉዳት ግልጋሎት አይሰጡም ተብሏል፡፡ ደያን ሎቭረን ለግጥሚያው ብቁ የማይሆን ከሆነ የርገን ክሎፕ ፋቢንሆን በመሀል ተከላካይነት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ እየተነገረ ነው፡፡ ዤርዳን ሻኪሪ እና ጆርጂኒዮ ዊናልደም ወደ ልምምድ ተመልሰዋል፡፡

 

 

የባየርኑ ጄሮም ቦአቲንግ ወደ ሜዳ ሊመለስ እንደሚችል የተነገረ ሲሆን ኪንግስሊ ኮማንም በጨዋታው ሊሰለፍ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

 

 

የስፔኑ ባርሴሎና ደግሞ ወደ ፈረንሳይ አቅንቶ በግሮፓማ ስታዲየም ከሊዮን ይፋለማል፡፡ የባርሴሎናው ተከላካይ ሳሙኤል ኡምቲቲተ ከጉዳት ተመልሶ የቀድሞ ክለቡን ይገጥማል የተባለ ሲሆን የሊዮኑ አጥቂ ናቢል ፈኪር በቅጣት፣ አማካዩ ታንጉይ ንዶምቤሌ ደግሞ በጉዳት ምክንያት የመሰለፉ ነገር አጠራጣሪ ነው ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *