የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሀገር ውጭ አዲስ የውድድር ቅርፅ ሊያዘጋጅ መሆኑን እወቁልኝ ብሏል፡፡
የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሀገር ውጭ አዲስ የውድድር ቅርፅ ሊያዘጋጅ መሆኑን እወቁልኝ ብሏል፡፡
አዲስ ይዘጋጃል የተባለው የውድድር አይነት በእንግሊዝ ኮሚዩኒቲ ሽልድ የምንለውን አይነት ሲሆን ሱፐር ኮፓ ዴ እስፓና የሚል ስያሜ እንደሚሰጠው ተነግሯል፡፡
የስፔን ፌዴሬሽን ላ ሊጋን በሌላው ዓለም ለማስተዋወቅ እና ገበያ ለማግኘት ሲሉ ወደ አሜሪካ ለመውሰድ ቢጥሩም አልተሳካም ፤ አሁን ደግሞ በአዲስ ቅርፅ ብቅ ብሏል፡፡
የስፔን የአሸናፊዎች አሸናፊ (ሱፐር ኮፓ) ስፔን ውስጥ በደርሶ መልስ ሁለት ግጥሚያዎች የሚደረጉ ሲሆን የ2018ቱ በባርሴሎና እና ሲቪያ መካከል ሞሮኮ ላይ ተካሂዶ ነበር፡፡
ሱፐር ኮፓ ዴ እስፓና በአራት ቡድኖች መካከል እንዲካሄድ የታሰበ ሲሆን የኮፓ ዴል ሬይ የፍፃሜ ተፋላሚ ቡድኖች እና የላ ሊጋ ሁለት ቀዳሚ ክለቦች ይካፈላሉ፡፡
የሮያል ስፔን አግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሊዩስ ሩቢያሌስ የሱፐር ኮፓ ዴ እስፓና የመጀመሪያው ውድድር በ2019 የስፔን ላ ሊጋ ከመጀመሩ አስቀድሞ እንዲደረግ ፍላጎት ቢኖራቸውም እስካሁን አልፀደቀም፡፡
ፕሬዚዳንቱ አዲሱ የውድድር ቅርፅ፤ በስፔን አግር ኳስ ላይ ተጨማሪ ፍላጎት እንዲመጣ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ቢቢሲ