አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ የዓለም የአንድ ማይል ክብረወሰንን አሻሻለ
አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ የዓለም የአንድ ማይል ክብረወሰንን አሻሻለ
በትናንትናው ዕለት ቦስተን ላይ በተካሄደው የአንድ ማይል የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ተካሂዶ 3፡47፡01 በመግባት አሸንፏል፡፡
ውድድሩን ከማሸነፍ ባለፈ እ.አ.አ በ1997 ዓ/ም በሞሮኳዊው ሂሳም ኤል ጉሩዥ ተይዞ የነበረውን የቦታውን የ3፡48፡45 ክብረወሰን በ1 ሰከንድ ከ44 ማይክሮ ሰከንድ ጊዜ አሻሽሏል፡፡
ዮሚፍ ሪከርድ ለመስበር ጥረቱን በማድረግ በሶስተኛው ተሳክቶለታል፤ ከዚህ በፊት የካቲት ወር ላይ በኒው ዮርክ የሚልሮዝ ጨዋታዎች ለ0.01 ማይክሮ ሰከንድ ዘግይቶ በመግባቱ አልተሳካለትም፤ በዚሁ የካቲት ወር የበርሚንግሃም የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ላይ እንዲሁ ሰፊ ግምት አግኝቶ የነበረ ቢሆንም በሀገሩ ልጅ ሳሙኤል ተፈራ ተቀድሞ አምልጦታል፡፡
አሜሪካዊው ጆኒ ግሬጎሪክ በ3፡49፡98 ሁለተኛ እንዲሁም ፕራኬል 3፡50፡ 94 ጊዜ ሶስተኛ መውጣት ችሏል፡፡