ቴህራን ለመካከለኛው ምስራቅ ከጠንካራ ሰዎች ይልቅ ጠንካራ ግንኙነት ያስፈልጋል አለች፡፡
ቴህራን ለመካከለኛው ምስራቅ ከጠንካራ ሰዎች ይልቅ ጠንካራ ግንኙነት ያስፈልጋል አለች፡፡
የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሀመድ ጃቫድ ዛሪፍ ለሳውዲ አረቢያ ችግራችንን በጠረጴዛ ዙሪያ እንፍታ የሚል መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት ነው ይህን ያሉት፡፡
ዛሪፍ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ በቀጠናው በርካታ ጠንካራ ሰዎች አሉን፤ ግንኙነታችን ግን የላላ ነው ብለዋል፡፡
ይሄ ደግሞ አንዱ በሌላው ላይ ጉልበቱን ለማሳየት ፍላጎት እንዲያድርበት አስተዋፅኦ አድርጓል ነው ያሉት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፡፡
ኢራን ከየትኛውም ጎረቤት ሀገር ጋር ጦርነት ውስጥ የመገግባት ዓላማውም ፍላጎቱም የላትም ያሉት ዛሪፍ አሁን እኛ የምንፈልገው ተቀራርቦ መነጋገርን እና በጋራ መስራትን ነው ብለዋል፡፡
ዛሪፍ በኛ በኩል ሳውዲ አረቢያን የማግለል አዝማሚያ ስላሳየን ሳይሆን ሪያድ ከኛ ጋር ለመነጋር ስላልፈለገች ነው በማለት በሁለቱ ሀገራት መካከል ላለው ቅራኔ መንስኤዋ ሳውዲ ናት የሚል አስያየት ሰጥተዋል፡፡
እናም ሳውዲ ከኢራን ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ከሆነች በኛ በኩል ችግር የለም ለውይይት በራችን ክፍት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ኢራን የሳውዲ ደህንነት የራሷም ደህንነት አድርጋ እንደምታምነው ሁሉ ሪያድም ሁኔታውን በዚህ ደረጃ ልትረዳው ይገባል ሲሉም ሁለቱ ሀገራት ስኬታችም ውቀታቸውም የጋራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
መንገሻ ዓለሙ