በዩሮ 2020 የማጣሪያ ጨዋታዎች እንግሊዝ እና ፈረንሳይ በድል ጎደና ላይ እየተጓዙ ነው፡፡
ለአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ተሳታፊ ለመሆን የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡
እንግሊዝ ወደ ሞንቴኔግሮ አቅንታ 5 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ድል አድርጋለች፡፡ ሃሪ ኬን እና ሮዝ ባርክሌ እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ኪን ቀሪዋን ማስቆጠር ችሏል፡፡ ሶስቱ አናብስት ምድቡን በስድስት ነጥብ ይመራሉ፡፡
ፈረንሳይ ፓርክ ደ ፕሪንስ ላይ አይስላንድን ሳሙኤል ኡምቲቲ፣ ኦሊቪዬ ዥሩ፣ ክሊያን ምባፔ እና አንቱዋን ግሪዝማን 4 ለ 0 በማሸነፍ ምድቡ አናት ላይ በስድስት ነጥብ ተቀምጧል፡፡
ፖርቱጋል ደግሞ ዳ ሉዝ ላይ ከሰርቢያ አቻዋ ጋር በ1 ለ 1 አቻ ውጤት ተለያይታለች፤ ፖርቱጋል በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ስትለያይ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጉዳት አስተናግዷል፡፡
በሌሎች ጨዋታዎች ዩክሬን ከሜዳዋ ውጭ ሉግዘምበርግን 2 ለ 1 ድል ስታደርግ፤ ኮሶቮ ከቡልጋሪያ 1 ለ 1፤ አልባኒያ 3 ለ 0 አንዶራ ተለያይተዋል፡፡
ዛሬ የሌሎች ምድቦች የማጣሪያ ጨዋታዎች ሲደረጉ ምድብ D ላይ ሲውዘርላንድ ከ ዴንማርክ፤ ሪፐብሊክ አየርላንድ ከ ጆርጂያ ይፋለማሉ፡፡
በምድብ F በተመሳሳይ 4፡45 ላይ የማጣሪያ ግጥሚያዎች ሲደረጉ፤ ስፔን ወደ ማልታ አቅንታ ትጫወታለች፤ ኖርዌይ ከ ስዊድን እና ሮማኒያ ከ ፋሮ አይስላንድስ ይገናኛሉ፡፡
በምድብ J ደግሞ ጣሊያን በእስታዲዮ ኢኒኖ ታርዲኒ ምሽት 4፡45 ሲል ሌችተንስታን ስታስተናግድ፤ ቦስኒያ ሄርዜጎቪና ግሪክን ትገጥማለች፤ አርሜኒያ ከ ፊንላንድ በተመሳሳይ ጊዜ ይጫወታሉ፡፡