ግለሰቡ የአሜሪካ ዶላር እና ሌሎች የውጭ ሀገራት ገንዘቦች ጫማ ውስጥ ደብቆ ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር ተያዘ፡፡
ግለሰቡ የአሜሪካ ዶላር እና ሌሎች የውጭ ሀገራት ገንዘቦች ጫማ ውስጥ ደብቆ ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር ተያዘ፡፡
በዛሬ የምንዛሪ ዋጋ 637,128.923 ብር የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች ጫማ ውስጥ በመደበቅ ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር ዛሬ ከጠዋት 2፡00 አካባቢ ቶጎጫሌ ኬላ ላይ በጉምሩክ ፈታሾች ተይዝዋል፡፡
ኡስማን ገረመው የተባለ ተጠርጣሪ 18 ሺህ 838 የአሜሪካ ዶላር፣ 270 ፓውንድ፣ 2ሺህ ዩሮ፣ 1 ሺህ 600 የሳውዲ ሪያል እና 25ሺህ 550 የዩናይትድ አረብ ድርሀም ጫማ ውስጥ ደብቆ ከሀገር ለማስወጣት ሲሞክር መያዙን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡