የማላዊ ፕሬዝዳንት ህዝቡን አንድ እድል ብቻ ስጡኝ እያሉ ነው፡፡
የማላዊ ፕሬዝዳንት ህዝቡን አንድ እድል ብቻ ስጡኝ እያሉ ነው፡፡
ማላዊ በመጭው ግንቦት ወር በምታካሂደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሀገሪቱን በመምራት ላይ ያሉት ፒተር ሙታሪካ ለሁለተኛ ጊዜ ይወዳደራሉ፡፡
እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2014 ወደ ስልጣን የመጡት ሙታሪካ በደጋፊዎቻቸው ፊት ቆመው ቅስቀሳ ሲያደርጉ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እድሉን ስጡኝ እንጅ ዳግም አላስቸግርም የሚመስል ንግግር አድርገዋል፡፡
አሶሸትድ ፕሬስ እንደዘገበው ሙታሪካ በምርጫው የቀድሞው ምክትላቸውን ጨምሮ በጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ብርቱ ፉክክር ይጠብቃቸዋል፡፡
እስንካሁን በዚህች ሀገር ታሪክ ተሰርተው የማያውቁ ስራዎችን ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ አከናውነናል ያሉት ሙታሪካ ማላዊን ከድህነት ወደ ተስፋ ምድርነት ለመቀየር ተዘጋጂተናል ብለዋል፡፡
ለተቃዋሚዎች ባስተላለፉት መልእክት ኑ እና በጋራ ሀገራችንን እንገንባ ምክንያቱም ሀሳባችሁ ከኛ የተለየ ሆኖ አላገኘንውም ነው ያሉት፡፡
መንገሻ ዓለሙ