ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የሱዳን ሪፐብሊክ ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት አባል በሆኑት በጄነራል ጋላሌዲን አል ሼኽ ከተመራው የልኡካን ቡድን አነገገሩ፡፡
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የሱዳን ሪፐብሊክ ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት አባል በሆኑት በጄነራል ጋላሌዲን አል ሼኽ ከተመራው የልኡካን ቡድን አነገገሩ፡፡
ጄነራል ጋላሌዲን ለጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በሱዳን ስላለው ጠቅላላ ሁኔታ ያስረዱ ሲሆን ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግንኙነት ስልታዊ እንደሆነ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥትም ለሱዳን የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው መንግሥታቸው ለሱዳን ሕዝቦች የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል ገልጸው፤ ይህም ሉዓላዊነትን ባከበረና ጣልቃ ገብነትን ባስወገደ መልኩ ይሆና ብለዋል፡፡
በመልእክታቸውም ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ ሽግግሩን ሰላማዊ ለማድረግ ቅሬታን ፈችና የሕዝቡን ጥያቄ መላሽ በሆነ መልኩ እንዲንቀሳቀስ አበረታትተዋል።
ምንጭ፤-ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት