loading
በኢትዮጵያ ዋንጫ ኢትዮጵያ ቡና በፎርፌ ውጤት ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ

በ2011 ጥሎ ማለፍ ዋንጫ/ የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ግጥሚያ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከስሑል ሽረ ጋር ይጫወቱ ነበር፡፡ እንግዳው ስሑል ሽረ ቡድን ግን ከጨዋታው ቀን ቀደም ብሎ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ የእግር ኳስ ክለቡ የጥሎ ማለፍ ጨዋታውን ላለማካሄድ መወሰኑን አሳውቋል።

በትናንትናው ዕለት ስብሰባውን ያካሄደው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ኮሚቴ የዛሬው ጨዋታ እንዳይካሄድ በመወሰን ኢትዮጵያ ቡና ወደ ቀጣዩ ዙር ወይንም ግማሽ ፍፃሜ በፎርፌ ውጠየት እንዲያልፍ ወስኗል ሲል ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

ስሑል ሽረዎች ከውድድሩ ራሳቸው ያገለሉበት ምክንያት ባጋጠማቸው የፋይናንስ ችግር መሆኑ ተነግሯል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *