loading
የሉሲዎቹ አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ አደረገች::

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) ከጋምቢያ አቻቸው ጋር ላለባቸው የወዳጅነት ጨዋታ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጓን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ድረ ገፅ ይፋ አድርጓል።

በጋምቢያ ባካው ከተማ ላይ ሰኔ 8 እና 11 ሉሲዎቹ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። ለዚህም እንዲረዳት አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ለተጫዋቾች ጥሪ አድርጋለች።

ከግብ ጠባቂዎች

የጥረት ኮርፖሬቷ ታሪኳ በርገና፤ የሀዋሳ ከተማው አባይነሽ ኤርቄሎ፤ የመከላከያዋ ማርታ በቀለ ጥሪ ደርሷቸዋል፡፡

በተከላካይ መስመር

መስከረም ኮንካ፣ ናርዶስ ጌትነት፣ እጸገነት ብዙነህ፣ ነጻነት ጸጋዬ ከአዳማ ከተማ፤ ገነሜ ወርቁ እና ብዙአየሁ ታደሰ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ መሰሉ አበራ ከ መከላከያ እና የሐዋሳ ከተማዋ ቅድስት ዘለቀ ተመርጠዋል፡፡

ከአማካኝ ተጫዋቾች ደግሞ ህይወት ደንጊሶ እና ብርቱካን ገ/ክርስቶስ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ከመከላከያ እመቤት አዲሱ እና አረጋሽ ካልሳ፤ አለምነሽ ገረመው ከኢትዮ ኤሌክትሪክ፤ ሰናይት ቦጋለ ከአዳማ ከተማ እንዲሁም ይመችሽ ዘውዴ ከድሬዳዋ ከተማ ተካትተዋል፡፡

በአጥቂ ስፍራ

ሎዛ አበራ፣ ገነት ሀይሉ፣ ሴናፍ ዋቁማ እና ሰርክአዲስ ጉታ ከአዳማ ከተማ፤ መዲና ጀማል እና ሔለን እሸቱ ከመከላከያ እና ምርቃት ፈለቀ ከሀዋሳ ከተማ ጥሪ ተደርጎላቸዋል ተብሏል፡፡

ጥሪ የደረሳቸው እነዚህ ተጫዋቾች በነገው ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *