loading
የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት በተማሪዎች ሞት አዝኛለሁ አለ፡፡

የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት በተማሪዎች ሞት አዝኛለሁ አለ፡፡

የሽግግር ምክር ቤቱ መሪ ጄኔራል አብደልፈታህ አልቡርሀን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በሰሜናዊ ኮርዶፋን አል ኦቤይድ ከተማ የተፈፀመው የአምስት ተማሪዎች ግድያ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ተማሪዎቹ የነዳጅ እና የዳቦ ዋጋ አሻቀበ በሚል ምክንያት ለተቃውሞ አደባባይ በመውጣታቸው ነው በፀጥታ ሀይሎች የተገደሉት፡፡

አልቡርሀን ድርጊቱ ወንጀል መሆኑን በመግለፅ ጉዳዩ በአስቸካይ ተጣርቶ በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ተቃዋሚዎቹ በወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ ምክትል ሀላፊ ጄኔራል ሞሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ እዝ ስር የሚንቀሳቀሰው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ነው ይህን ግድያ የፈፀመው ሲሉ ይከሳሉ፡፡

ዳጋሎ ግን ይህ በሚሆንበት ጊዜ ለስራ ጉብኝት ወደ ካይሮ አቅንተው ከፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ጋር እየተወያዩ ነበር ተብሏል፡፡

ምክር ቤቱ ይህን መግለጫ የሰጠው ተቃዋሚዎቹ በቅርቡ በሲቪል መንግስት ምስረታ ዙሪያ ከጄኔራሎቹ ጋር ሊያደርጉት የነበረውን ውይይት መሰረዛቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው የሚል ዘገባ በሰፊው እየተሰራጨ ነው፡፡

መንገሻ ዓለሙ

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *