loading
በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃያ አንድ ሺህን ተሻገረ፡፡

አዲስ አበባ፣ግንቦት 18፣2012 በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃያ አንድ ሺህን ተሻገረ፡፡

በአህጉረ  አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር እያደገ በመምጣት አሁን ላይ 121ሺን የተሻገረ ሲሆን በወረርሽኙ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሶስት ሺን ማለፉን የአፍሪካ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠሪያ ማዕከል ሲዲሲ ይፋ አድርጓል፡፡ማዕከሉ ማክሰኞ እለት ባወጣው ሪፖርት በአፍሪካ ተጨማሪ ከ46 ሺህ በላይ ሰዎች በኮቪድ 19 ቫይረስ መጠቃታቸውን አረጋግጧል፡፡የማዕከሉ መረጃ እንደሚያሳየው በወረርሽኙ በከፍተኛ ደረጃ ከተጠቁት ሀገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ ከ23 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁባት ሲሆን ግብጽ ከ17 ሺህ በላይ ሰዎች፣  አልጄሪያና ናይጄሪያ ከ8 ሺህ በላይ እንዲሁም ሞሮኮ ከ7 ሺ 5መቶ በላይ ዜጎቻቸው በቫይረሱ ተጠቅተውባቸዋል፡፡የአፍሪካ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠሪያ ማዕከል ሲዲሲን መረጃ ዋቢ በማድረግ ሽኑዋ እንደዘገበው በቫይረሱ ስርጭትም ሆነ በሟቾች ቁጥር ሰሜናዊ የአፍሪካ ቀጠና ከፍተኛውን ስፍራ ይዟል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *