ፔፕሲኮ ኢትዮጵያ “ ምግብ ይለግሱ -ተስፋን ይቀጥሉ “የሚል ፕሮግራም ይፋ አደረገ ፡፡
አዲስ አበባ ፣ግንቦት 27፣ 2012 ፔፕሲኮ ኢትዮጵያ “ ምግብ ይለግሱ -ተስፋን ይቀጥሉ “የሚል ፕሮግራም ይፋ አደረገ ፡፡በፕሮግራሙም 2 ሺህ ሰዎችን ለሶስት ወራት ምሳና እራት እንዲመገቡ ይደረጋል፡፡ድርጅቱ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንደስታወቀዉ ፤ ድጋፉ በኢትዮጵያ በኮቪድ 19 ስርጭት ምክንያት ለተጎዱና ጫና ለደረሰባቸዉ አካላት የሚዉል ሲሆን 8ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡ድርጅቱ ድጋፉን ከሜቅዶንያ በጎ አድራጎት ተቋም ጋር በመተባበር እንዳደረገዉም ገልጿል፡፡ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የፔፕሲኮ መጠጦች ዋና ስራ አሰኪያጅ የሆኑት ሰርጂኦ ፓያ ‘’ምግብ ይለግሱ -ተስፋን ይቀጥሉ‘’ የተሰኘዉን ፕሮግራም የቀረጽነዉ በወረርሽኙ ሳብያ ጉዳት ለደረሰባቸዉ ኢትዮጵያዉያን የማህበረሰብ ክፍሎች በአስፈላጊዉ ድጋፎች ለመድረስ ነዉ ብለዋል፡፡በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ዉስጥ ካሉ ምግብ እና መጠጥ አምራቾች አንዱ የሆነዉ ድርጅታችን በወረርሽኙ ምክንያት ለተጎዱ ምግብና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎች ማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት እንደሚያምን ስራ አስክያጁ ገልጸዋል፡፡የፔፕሲኮ ምርቶች በዓለም ላይ ከ200 በላይ ሀገራት በቀን ለአንድ ቢሊየን ግዜ ግልጋሎት ላይ እንደሚዉልም ከድርጅቱ ሰምተናል