loading
ከ1ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የላብራቶሪ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2012  ከ1ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የላብራቶሪ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገ:: የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ ሬይ አስመጪ እና ላኪ ኃ/ተ/ግ/ድርጅት በዛሬ ዕለት ለኮሮና መከላከያ የሚውሉ የላብራቶሪ መመርመሪያ መሳሪያዎች ለ ሚኒስቴሩ አስረክበዋል ፡፡
በርክክቡም ወቅት የጤና ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ያዕቆብ ሰማን እንደተናገሩት የተደረገው ድጋፍ ለኮሮና በሽታ ለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከሎች አገልግሎት የሚውል መሆኑን በመጥቀስ የኮሮና ወረርሽኝን በመከላከል እና በመቆጣጠር ረገድ የሚገጥመንን የላብራቶሪ መመርመሪያ መሳሪያዎች እጥረት ለመቅረፍ ጉልህ አስተዋፅኦ ያላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም መሳሪያዎቹ የጤና ባለሙያዎች በቀላሉ ሊገለገሉባቸው የሚችሉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
የሬይ አስመጪ እና ላኪ ኃ/ተ/ግ/ድርጅት ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት ዮርዳኖስ ብርሃኑ እንደተናገሩት፤ ለጤና ሚኒስቴር ያስረከቡዋቸው የላብራቶሪ መመርመሪያ መሳሪያዎች እና የህክምና መገልገያ እቃዎች በማንኛውም ሁኔታ መጠቀም እና የጤና ምርመራ ውጤቶችን በፍጥነት ለማወቅ የሚያስችሉ መሆናቸውን የተናገሩ ሲሆን፤ በተጨማሪም በኮሮና ምክንያት በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ያሉ ታካሚዎች በተያያዥነት ያሉባቸውን ህመሞች ለመመርመር የሚረዱ ናቸው ብለዋል፡፡ በቀጣይ ኮሮናን በመከላከል እና በመቆጣጥር ረግድ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ ፤- የጤና ሚኒስቴር

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *