loading
 በፌደሬሽን ም/ቤት ፤በህግ ትርጉም ሽፋን የተላለፈዉን የፖለቲካ ዉሳኔ እንደሚቃወም ባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ገለጸ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012 በፌደሬሽን ም/ቤት ፤በህግ ትርጉም ሽፋን የተላለፈዉን የፖለቲካ ዉሳኔ እንደሚቃወም ባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ገለጸ::ፓርቲዉ ለአርትስ ባለከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ፤የፌደሬሽን ምክርቤት በሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ/ም ባደረገዉ ስብሰባ ፤6ኛዉ አገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ በዉል ላልታወቀ ዘመን እንዲራዘም እና እድሜያቸዉ መስከረም 30 ቀን 2012 ዓ/ም የሚያበቃላቸዉ ሁሉም ም/ቤቶች በስልጣናቸዉ እንዲቀጥሉ መወሰኑ አግባብንት የለዉም ብለዋል፡፡ የባልደራስ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰፊ ምክክር አድርጎ ከመነሻዉ ገዢዉ ፓርቲ ለአገራችን የሚጠቅም የፖለቲካ አማራጭ ያላቸዉን ፖለቲካ ፓርቲዎች ሙሉ በሙሉ ያገለለ ነዉ ብለዋል፡፡ዉሰኔዉም አገራችን ያለችብትን ዉስብስብ ወቅታዊ ሁኔታ በቅጡ ያላገናዘበ እና በቀጣይ ም ከባድ አደጋ የሚጋብዝ አካሄድ እንደሆነ ፓርቲያችን ተገንዝቧል ብሏል ፓርቲዉ በመግለጫ፡፡ ፓርቲዉ በፌደሬሽን ምክርቤት ዉሳኔ የተጀመረዉ ሂደት የመጨረሻ ዉጤት ተረኛ ፈላጭ ቆራጭ ስርዓት የሚፈጥር ነዉ ብሏል፡፡ባልደራስ በመግለጫዉ የሀገራችንን ህልዉና ለማስቀጠልና ወደሀቀኛ ዲሞክራሲ ለመሻገር ፤ለአንድነት ሃይሎች ፤በዉጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንንና ትዉልደ ኢትጵያዉያን እና ለአለም አቀፍ ማህበረስብ ጥሪ አድርጓል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *