loading
በኮሮና ዙርያ የተሰሩ ከ20 በላይ ጥናቶች በኦን ላይን ኮንፈረንስ ለውይይት በመቅረብ ላይ ናቸው ።

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2012 በኮሮና ዙርያ የተሰሩ ከ20 በላይ ጥናቶች በኦን ላይን ኮንፈረንስ ለውይይት በመቅረብ ላይ ናቸው ።የኦንላይን ኮንፍረንሱ ምሁራን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ ያከናወኑዋቸው ጥናቶች ለማሳወቅና ቫይረሱን አስመልክቶ የእውቀት ሽግግር ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።ውይይቱ ላይ የመቐለ አዲስ አበባ ፣ ባህርዳር እና ሃረማያ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን የተሳተፉበት መሆኑን ዶክተር አዲሱ ተናግረዋል ።ጥናታዊ ጽሁፎቹ ህብረተሰቡ በኮሮና ቫይረስ ላይ ያለው ግንዛቤ፣ የህክምና ባለሙያዎች ቫይረሱን ለመከላከል ያላቸው ዝግጅነትና የሚገጥሙዋቸው ችግሮች፣ቫይረሱን  ለመከላከል ባህላዊ መድሃኒቶች እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያመላክቱ ናቸው ብለዋል ።

አብዛኛው ህብረተሰብ በመገናኛ ብዙሃን በሚተላለፉ መልእክቶች አማካኝነት ስለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተሻለ ግንዘቤ እንዲኖረው በማድረጉን በጥናቶቹ ተጠቅሷል ።ግንዛቤው ወደ እውቀት በመቀየርና በአተገባበር ላይ ያለው ችግር ቀጣይ ስራ እንደሚፈልግም በጥናቱ ተጠቁሟል ።ኮሮና ለመከላከልና በቫይረሱ የተያዙ የማህበረሰብ ክፍሎች ለማከም በጤና ባለሞያዎች ያለው ዝግጁነት አጥጋቢ ሆኖ አልተገኘም ተብሏል።በመሆኑም የጤና ባለሙያዎች ራሳቸውን ከቫይረሱ ለመከላከልና የታመመውን ለማከም ያላቸውን የዝግጁነት ማነስ በቀጣይ መስከተካከል አለበት የሚል ምክረ ሃሳብ ቀርቧል ።መምህር ግዛቸው አገሪቱ ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል እየሄደችበት ያለው ስርአት ምን ይመስላል በሚል ዙሪያ ባቀረቡት ጥናት እንዳመለከቱት በለይቶ ማቆያ ማእከላት  የሚገኙ ወገኖች በስድስት ቀናት ውስጥ የጤንነታቸው ሁኔታ ማወቅ እንደሚቻል ዓለም አቀፍ ጥናቶች ዋቢ በመጥቀስ አብራርተዋል ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *