loading
ዝክረ ሰኔ 15 የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለተሰዉ ከፍተኛ አመራሮች 1ኛ ዓመት መታሰቢያ ተከናወነ ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 15 ፣ 2012  ዝክረ ሰኔ 15 የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለተሰዉ ከፍተኛ አመራሮች 1ኛ ዓመት መታሰቢያ ተከናወነ ፡፡በሰኔ 15 ቀን 2011ዓ.ም ለተሰዉ ከፍተኛ አመራሮች የ1ኛ አመት መታሰቢያ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ተካሂዷል። ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ እና የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ እንዲሁም የተለያዩ አመራሮችና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተገኝተዉ ነዉ መርሃ ግብሩን ያከናወኑት ፡፡በመርሃ ግብሩ ላይ ከ 1200 በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን የተሰዉ ወገኖችን በዚህ መልኩ ማሰቡና ጠቃሚ የሆነ ተግባር ማከናወን እንደ ሀገር ወደ ፌት ሊያስኬድ የሚችል መሆኑ ተነግሯል፡፡

መረጃዉን ያገኘነዉ ከከንቲባ ፅ/ቤት ነዉ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *