loading
ኢንጂኔር ታከለ ኡማ በከንቲባነት ዘመናቸው ላደረጉላቸው ድጋፍ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን አመሰገኑ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 ኢንጂኔር ታከለ ኡማ በከንቲባነት ዘመናቸው ላደረጉላቸው ድጋፍ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን አመሰገኑ:: ከአዲስ አበባ ከንቲባነት ቦታቸው ተቀይረው የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ሆነው የተሸሙትምክትል ከንቲባው በነበራቸው የሁለት ዓመት የሥራ ዘመን የከተማዋ ነዋሪዎች እና የስራ ባለደረቦቻቸው ድጋፍ እንዳልተለያቸው በፅህፈት ቤታቸው ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ላይ አስፍረዋል፡፡ በታሪክ አጋጣሚ ይህችን ታሪካዊ ከተማ ለመምራት የተገኘውን ትልቅ ዕድል ላለማባከን እና ውጤታማ ስራ ለማከናወን ጥረት ማድረጋቸውንም ገልፀዋል፡፡

ኢንጂኔር ታከለ በፅሁፋቸው አዲስ አበባን እንደስሟ ለማድረግ በደስታ፣ በፍላጎትና በፍቅር በሚደረገው ጥረት ምርኩዝ ለሆናቸሁኝ አዲስ አበቤዎች ከልቤ አመሰግናለሁ፤ ላጎደልናቸው ስራዎች ደግሞ በፍፁም ቅንነት ይቅርታ እጠይቃለሁ ብለዋል፡፡ አዲስ አበባን ያክል ትልቅ ከተማ የመምራት ዕድል በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ ያሉት ኢንጂኔር ታከለ ለአዲሱ ካቢኔ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *