loading
አንድ የቻይና ከፍተኛ ዲፒሎማት በሁለቱ ኮሪያዎች ጉዳይ ለመምከር ወደ ደቡብ ኮሪያ ሊጓዙ ነው::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13፣ 2012 አንድ የቻይና ከፍተኛ ዲፒሎማት በሁለቱ ኮሪያዎች ጉዳይ ለመምከር ወደ ደቡብ ኮሪያ ሊጓዙ ነው:: በሰሜን እና ደቡብ ኮሪያዎች መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተባባሰ የመጣው ውጥረት ተሟሙቆ የነበረውን አዲስ ግንኙነት ጥላ አጥልቶበታል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በድንበር አካባቢ ቀለል ያለ የተኩስ ልውውጥ እስከማድረግ ያደረሳቸው ግጭት ውስጥ መግባታቸው ሳያንስ ለሽምግልና በሮቻቸውን መዝጋታቸውም ስጋቱን ከፍ አድርጎታል፡፡ ከሴኡል የወጣው መግለጫ እንደሚያየው የቻይናው ኮሚኒስት ፓርቲና የምክር ቤት አባል ያንግ ጂዬቺ
በሁለቱ ኮሪያዎች እንዲሁም በቀጠናው የሰላም ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግስት ጋር ይመክራሉ፡፡ ቻይናና ደቡብ ኮሪያ ጃፓንን ያካተተ ዓመታዊ የሶስትዮሽ ጉባኤ ለማድረግ በሚያስችል አጀንዳ ላይም እንደሚመክሩ የፕሬዚዳንት ሺ ዢምፒንግ ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ቻይና የሰሜን ኮሪያ ዋነኛ አጋር ስትሆን ፒዮንግያንግና ዋሽንግተን ጀምረውት የነበረው የኒውክሌር ስጋትን የመቀነስ ድርድር እንዲሳካ ቀላል የማይባል ሚና እንነበራት ይነገራል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *