loading
የማሊ ተቃዋሚዎች በሀገሪቱ አዲስ ምርጫ እንደሚካሄድ ማረጋገጫ እየሰጡ ነው::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 14፣ 2012  የማሊ ተቃዋሚዎች በሀገሪቱ አዲስ ምርጫ እንደሚካሄድ ማረጋገጫ እየሰጡ ነው:: በማሊ መፈንቅለ መንግት መካሄዱን ተከትሎ አለመረጋጋት እንዳይፈጠር እና ህዝቡ ወደብጥብጥ እንዳይገባ ከፍተኛ ስጋት ተፈጥሯል፡፡ ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንት ቡበከር ኬታን እና ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን በቁጥጥር ስር ያደረገው የሀገሪቱ
ጦር ሃይል ስጋት አይግባችሁ አዲስ ምርጫ ተካሂዶ ማሊ ወደ ቀድሞ ሰላሟ ትመለሳለች ብለዋል፡፡

ሲ ጂ ቲ ኤን እንደዘገበው ለወራት ፕሬዚዳንቱን በመቃወም የአደባባይ ሰልፎችን ሲያካሂዱ የቆዩት ተቃዋሚዎች የኬታን ከስልጣን መነሳት በፀጋ ቢቀበሉትም በርካታ ሀገራትና ተቋማት እያወገዙት ይገኛሉ፡፡ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ መፈንቅለ መንግሰቱን አውግዘው በአስቸኳይ በሲቪል አስተዳደር መቀየር አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በፕሬዚዳንቱ ላይ እርምጃውን የወሰዱት ራሳቸውን ብሄራዊ የህዝብ ማዳን ኮሚቴ ብለው የሚጠሩ ሃይሎች ቀጣዩ የሀገሪቱ እጣ ፋንታ ብዙም አያሳስብም ሁሉም ነገር ይስተካከላል ብለዋል፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማትም በማሊ የተፈጠረው ችግር ከራሷ አልፎ ለቀጠናው እንዳይተርፍ ስጋታቸውን እየገለፁ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *