loading
በኮቪድ 19 ምክንያት በአፍሪካ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ 40 ሺ አለፈ:

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 በኮቪድ 19 ምክንያት በአፍሪካ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ 40 ሺ አለፈ:: የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ ባደረገዉ መረጃ ደቡብ አፍሪካ ከ18 ሺ 656 በላይ ዜጎቿን በኮቪድ 19 ምክንያት በማጣት በአሁጉሪቱ ቀዳሚ ሀገር ናት፡፡ አሁን ላይ በአፍሪካ አህጉር በአጠቃላይ በወረርሽኙ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ40 ሺ አልፏል፡፡ 6 ሺህ አንድ መቶ አርባ ሁለት ዜጎቿ በቫይረሱ የሞቱባት ግብፅ በአሀጉሪቱ በሞት ብዙ ዜጎቻቸዉን
ካጡ ሀገራት ሁለተኛ ሀገር ስትሆን ሞሮኮ በሶስተኛናት ትከተላለች፡፡

ኢትዮጵያ ፣ ናይጄሪያና አልጄሪያ ከ1 ሺ በላይ ሰዎችን በቫይረሱ ምክያት በማጣት 4ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ነዉ ያለዉ ድርጅቱ ፡፡ በብሩንዲና በኮሞሮስ ከ 10 ሰዎች በታች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መሞታቸው የተገለጸ ሲሆን ኤርትራና ሲሼልስ ደግሞ እስካሁን በቫይረሱ ምክንያት አንድም የሞት ሪፖርት አላቀረቡም፡፡ ባለፉት 90 ቀናት ዉስጥ አፍሪካ ቫይረሱን ከመከላከል አንፃር ወደ ታች እያሽቆለቆለች መሆኑን የገለፀዉ የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በተመለከተ የአፍሪካ ሀገራት ጥንቃቄዉን አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ አሳስቧል ፡፡ አንዳንድ ሀገሮች ከቫይረሱ ስርጭት አንፃር በከፍተኛ ሁኔታ ለዉጥ እያመጡ ቢሆንም አፍሪካ ግን በተቃራኒ ሁኔታ በቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ቁጥር እያስመዘገበች መሆኑ ነዉ የተነገረዉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *