loading
በሕዳሴ ግድቡ የሦስትዮሽ ድርድር የአፍሪካ ሕብረት ባለሞያዎች ሚና ከፍ ይበል በሚለው የኢትዮጵያ ሐሳብ ግብጽ ሳትስማማ መቅረቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 በሕዳሴ ግድቡ የሦስትዮሽ ድርድር የአፍሪካ ሕብረት ባለሞያዎች ሚና ከፍ ይበል በሚለው የኢትዮጵያ ሐሳብ ግብጽ ሳትስማማ መቅረቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ::በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያ የአፍሪካ ህብረት ባለሙያዎች ሚና ከፍ ይበል በሚለዉ ዙሪያ ግብፅ እንዳልተስማማች የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሃሳቡ ላይ ሱዳን ስትስማማ ግብጽ ሳትቀበል መቅረቷን ነዉ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የገለጸዉ፡፡ኢትዮጵያ የአፍሪካውያን ችግሮች በአፍሪካ እንዲፈታ የያዘችውን አቋም አጠናክራ እንደምትቀጥል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ገልጿል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመገናኛ ብዙሀን በሰጠዉ መግለጫ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ባለፉት ሳምንታት የተለያዩ ሥራዎች መከናወናቸውንም አሳውቋል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሳምንቱ የጅቡቲ እና የደቡብ ሱዳን የልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት መካሄዱን በጋዜጣዊ መግለጫው አሳውቀዋል።በዚህም ከጅቡቲ ጋር በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ዙሪያ ምክክር መካሄዱን ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል የጃፓን እና የሕንድ አምባሳደሮች በዚህ ሳምንት የሹመት ደብዳቤያቸውን ማቅረባቸውን የገለጹት ቃል አቀባዩ፣ ጃፓን በኢትዮጵያ ሴቶችን በማብቃት ዘርፍ ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል።ከ580 በላይ የሚሆኑ የሕንድ ኩባንያዎች ደግሞ በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ተሳትፈው እንደሚገኙ ነው ቃል አቀባዩ የገለጹት።

በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲውም ከሳዑዲ ዓረቢያ እና ከቤይሩት ከ600 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውንም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።ከወቅታዊ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሁሉም የጎረቤት ሀገራት እና አሜሪካን ጨምሮ የኢትዮጵያ ሰላምን የሚፈልጉ ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን ተናግረዋል

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *