በየመን ለደረሰው ቀውስ ዓለም ዝምታን መምረጡ እንዳሳሰበው የመንግስታቱ ድርጅት ገለፀ::
አዲስ አበባ፣ ህዳር 03፣ 2013 በየመን ለደረሰው ቀውስ ዓለም ዝምታን መምረጡ እንዳሳሰበው የመንግስታቱ ድርጅት ገለፀ:: ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት በየመን በእርስበርስ ውጊያ ሳቢያ የተከሰተው ርሃብ እድሚያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ 100 ሺህ ህፃናትን ህይዎት አደጋ ላይ ጥሏል፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጠቅሶ እንደዘገበው ሁኔታው በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ የመን በዚህ ችግር ምክንያት አንድ ትውልድ ልታጣ ትችላለች፡፡
መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ በየመን 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚሆኑ ህፃናት በአደገኛ ሁነታ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የመንግስታቱ ድርጅት ህጻናቱ ከገበቡበት ችግር እንዲወጡ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝምታውን በስበርና የድጋፍ እጁን መዘርጋት አለበት ሲል ጥሪውን አቅርቧል፡፡ የዓለም የምግብ ፕሮግራም በበኩሉ ከ24 ኪሊዮን በላይ የመናዊያን ዜጎች የጭከለት ደራሽ እርዳታ እንደሚፈልጉ በሪፖርቱ ይፋ አድርጓል፡፡ የመን ከገባችበት የእርስ በርስ ጦርነት እንድትወጣ ሁሉም የበኩሉን ጥረት ማድረግ አለበት ያለው የመንግስታቱ ድርጅት ይህን ማድረግ አንድን ትውልድ ከመጥፋት እንደማዳን ይቆጠራል ብሏል፡፡