loading
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ሰዉ በአንድ ቀን ከኮሮረና ቫይረስ ማገገሙ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ሰዉ በአንድ ቀን ከኮሮረና ቫይረስ ማገገሙ ተገለፀ፡፡ የጤና ሚኒስቴር በህዳር 21 ምሽት የ24 ሰዓቱን የኮሮና ቫይረስ ሁነታን በተመለከት በሰጠዉ መረጃ መሰረት በእለቱ በአንድ ቀን ዉስጥ አራት ሺህ አራት መቶ ዘጠና ሶስት ሰዎች ከኮረና ቫይረስ አገግገመዋል፡፡

ይህም እንደ አገር ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 73 ሺህ 8 መቶ 8 አድርሶታል ፡፡በእለቱ ከቫይረሱ ያገገሙት ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም ፤ የምርምራ አቅም መቀነሱን ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡ በኮሮና ቫይረስ እንደ አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል፡፡ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ በህዳር 21 ቀን በ24 ሰዓታ ዉስጥ ለ 4 ሺህ 8 መቶ 17 ሰዎች የላብራቶሪ ናሙና ምርመራ የተደረገላቸዉ ሲሆን 5 መቶ 40 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉ ተረጋግጧል፡፡ ይህም ባጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ከመቶ 10 ሺህ በላይ አድርሶታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *