loading
ዩዌሬ ሙሴቬኒ የምርጫው ቀን ከመድረሱ በፊት የማህበራዊ ትስስር ገፆችን እንዲዘጉ አዘዙ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 05፣ 2013 ዩዌሬ ሙሴቬኒ የምርጫው ቀን ከመድረሱ በፊት የማህበራዊ ትስስር ገፆችን እንዲዘጉ አዘዙ፡፡ ዩጋንዳ ጃኑዋሪ 14 ለምታካሂደው ምርጫ የተሳሳተ መረጃን በማሰራጨት ሁከት እንዲቀሰቀስ ያደርጋል በሚል ስጋት ከምርጫው ቀን አስቀድሞ ላሉት ሁለት ቀናት የበይነ መረብ አገልግሎት ዝግ ተደርጓል፡፡ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው የሀገሪቱ የኮምኒኬሽን ቁጥጥር ባለስልጣናትም የሙሴቬኒን ትእዛዝ ተቀብለው የበይነ መረብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን አገልግሎቱን እንዲዘጉ አድርገዋል፡፡

እንዲዘጉ ከተደረጉት የማህበራዊ ትስስር አገልግሎቶች መካከል ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ዋትስ አፕ እና ቫይበር ይገኙበታል፡፡ ሙሴቬኒ የማህበራዊ ድረ ገፆችን ተጠቅመው የፓርቲያቸውን ስም የሚያጠለሹ ያሏቸውን ወገኖች ጋጠወጥ በማለት ወርፈዋቸዋል፡፡ እንዱስትሪውን የሚያቀሳቅሱት አገልግሎት ሰጭዎች የዩጋንዳን መንግስት ውሳኔ መሰርተ ቢስና ከአጉል ፍርሃት የመነጨ ሲሉ አጣጥለውታል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስሙ በፖለቲካው እየገነነ የመጣውና ሙሴቬኒን አጥብቆ በመተቸት የሚታወቀውን ቦቢ ዋይን ከማክሰኞ ጀምሮ ሶሻል ሚዲያው መዘጋቱን አጥብቆ አውግዟል ህዝቡ ከመረጠ በኋላ ድምፁ እንዳይሰረቅበት ነቅቶ እንዲጠብቅም ጥርውን አስተላልፏል ነው የተባለው፡፡ የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን በበኩሉ መራጩ ድምፅ ከሰጠ በኋላ በፍጥነት ወደቤቱ መመለስ አለበት የሚል መሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ ፕሬዚዳት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ዩጋንዳን ማስተዳደር ከጀመሩ ከ34 ዓመት በላይ ያለፋቸው ሲሆን ዕድሜያቸው 76ትን ተሻግሯል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *