loading
አንግሊዝ የኮሮናቫይረስ የጉዞ ህግ የሚየጥሱ ግለሰቦች ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠነቀቀች ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 3፣ 2013 አንግሊዝ የኮሮናቫይረስ የጉዞ ህግ የሚየጥሱ ግለሰቦች ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠነቀቀች ፡፡ የእንግሊዝ መንግስት እንዳስታወቀው በተለይ የለይቶ ማቆያ ህግን ተላለፈው የተገኙ ተጓዦች ላይ ትኩረት ያደረገ ህግ ነው የደነገገችው፡፡ እንግሊዝ ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዞ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ብላ ከዘረዘረቻው ሀገራት ወደ ሀገሯ የሚገቡ ዜጎች ከበሽታው ነፃ መሆናቸው እስኪረጋገጥ በኳራንታይን ውስጥ እንዲቆዩ ያስገድዳል ህጉ፡፡

ይህን የጉዞ ታሪክ ደብቆ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ተጓዥ ግን 13 ሺህ 800 ዶላር የገንዘብ ቅጣትና 10 ዓመት እስር እንደሚጠብቀው የቦሪስ ጆንሰን መንግስት ይፋ አድርጓል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው የሀገሪቱ የጤናና ማህበራዊ ክብካቤ ባለስልጣናት አዲስ የወጣው ህግ ከፌብሩዋሪ 15 ጀምሮ ተፈፀሚ ይናሆል ብለዋል፡፡
ወደ እንግሊዝ የሚገቡ ሁሉም ተጓዦች ለ10 ቀናት በለይቶ ማቆያ ስፍራ የመግባት ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ለክትትል እንዲያመች ከኳራንታይን ሲወጡ የሚያርፉበትን ቦታና የተጠሪ አድራሻ ጭምር እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ፡፡

መንግስት በሽታውን ለመከላከል ከጀመራቸው እንቅስቃሴዎች መካከል ሆቴሎች የሚያከራይዋቸውን የአልጋ ቁጥሮች መወሰን የሚለው ይገኝበታል፡፡
ይህም የሆቴሉ ደንበኞች አካላዊ ርቀታቸው ተጠብቆ እንዲቆዩ ለማድረግ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *