loading
የሱዳን ተለዋዋጭ አቋም

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2013  ሱዳን የግድቡ ድርድር እንዲሳካ የአፍሪካ ህብረት መፍትሄ ሊያመጣ እንደሚችል ገለጸች::የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ህብረቱ በግድቡ ዙሪያ ያሉ አለመገባባቶችን በፍጥነት ለመፍታት በሚያደርገው ጥረት እምነት አለን ብሏል፡፡ ካርቱም በግድቡ ዙሪያ ያላትን አቋም ለማስረዳት የሱዳኗ የውጭ ጉደይ ሚኒስትር ማሪያም አልማሃዲ የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝታቸውን በይፋ ጀምረዋል፡፡ጉብኝቱ ከኬንያ ተጀምሮ ዲሞክራቲክ ኮንጎን በማካተት በአራት ሀገራት የሚደረግ ሲሆን በተለይ ከወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊመንበርና የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ሺኬሴዲ ጋር የሚደረገው ውይይት ትልቅ ትርጉም እንዳለው የሚኒስቴሩ መግለጫ ያሳያል፡፡

በዚህ ውይይት ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የውሃ ሙሌት ከመጀመሯ አስደቀድሞ ህጋዊ አስገዳጅነት ያለው ድርድር እንዲካሄድ ያለመ መሆኑን ሱዳን ትሪበዩን ዘግቧል፡፡
ሱዳን ከአሁን ቀደም የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ብቻውን በቂ አይደለም የፀጥታው ምክር ቤት፣ አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ይካተቱበት የሚል ሀሳብ አቅርባ በኢትዮጵያ በኩል ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ በመሊ መከራከሪያ ውድቅ መደረጉ የሚታወቅ ነው፡፡ በቅርቡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ የተመራ የግብፅ የልኡካን ቡድን በተመሳሳይ መንገድ ከኬንያ ጀምሮ ዲሞክራቲክ ጎንኮን ጨምሮ እስከ ቱኒዚያ የዘለቀ ተመሳሳይ ዓላማ ያለው ጉብኝት ማድረጉ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *