loading
ከአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባት ተከትበዋል ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 ከአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባት ተከትበዋል ተባለ:: የጤና ሚኒስቴር በየ24 ሰዓቱ በሚያወጣው የኮቪድ 19 ወቅታዊ መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባት መከተባቸውን ገልጿል፡፡
በተጨማሪም 2 መቶ22 ሺ 5 መቶ 60 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ሪፖርቱ አትቷል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አንደገለፀው ከሆነ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 4 ሺ 966 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 497 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ በአጠቃላይ እስካሁን በኮቪድ 19 የተያዙ ሰዎች ድምር ቁጥር 267 ሺ 597 ደርሷል። በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የ17 ሰዎች ህይወት ማለፉ የተነገረ ሲሆን 1ሺህ 109 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል ተብሏል፡፡ በአጠቃላይ በኮቪድ 19 ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 4 ሺ 38 መድረሱ ነው የተነገረው ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *