እነ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ በመጪው ጥር አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ አስታወቁ::
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 17፣ 2013 እነ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ በመጪው ጥር አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ አስታወቁ:: አምስት ኩባንያዎች እና ተቋማትን ያካተተው “ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ” የተሰኘው ጥምረት የሚያቋቁመው ኩባንያ፤ በኢትዮጵያ የቴሌኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት የማቅረብ ስራውን ከሰባት ወራት ገደማ በኋላ በጥር 2014 ዓ.ም ለመጀመር እንዳቀደ አስታወቀ።
አዲሱ ኩባንያ አሁን በሀገሪቱ በብቸኝነት የቴሌኮም አገልግሎት እየሰጠ ያለውን ኢትዮ ቴሌኮምን የሚገዳደር ነው ተብሎለታል። በኬንያው ሳፋሪኮም የሚመራው ጥምረት ይህን ያስታወቀው ትላንት ሰኞ ግንቦት 16 ባወጣው መግለጫ ነው። ጥምረቱ የኢትዮጵያ መንግስት የቴሌኮም አገልግሎት ፍቃድ ለመስጠት ያወጣውን ጨረታ ማሸነፉ በይፋ ከተገለጸ በኋላ መግለጫ ሲያወጣ የትላንቱ የመጀመሪያው ነው።